የሰው ልጅ በህይወቱ ደስተኛ ሆኖ ለማለፍ ሁሌም ሌት ተቀን ይታትራል:: እናት ከጫካ እንጨት መንጥራ አባት በህይወቱ መከራን ተሸክሞ ደከምኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለራሳቸው ተርበው ተጠምተው ታርዘው ልጃቸውን ለትልቅ ደረጃ ለማድረስ ይደክማሉ:: ታድያ ሁሉም ነገር አይሞናላቸውም:: በሌላኛው ህይወት ደግሞ ገና ጨቅላ ታዳጊ የሆኑ ተንከባካቢ የሌላቸው ድንገት በሚደርሱ አደጋዎች ምክንያት ጠግበው ሳይቦርቁ ወላጆቻቸውን አጥተው ደጋፊም ሳይኖራቸው ለጎዳና ይዳረጋሉ:: እድሚያቸው ቢገፋ ጉልበታቸው ቢከዳቸው የሰው እጅ ላይ የሚወድቁ እናት እና አባቶች ልጃቸውን ሲጦሩ ከፊሉ ደጋፊና አቃፊ አጥቶ በረሃብ እና በበሽታ ይጠቃል። ተማሪውም መማርን ሽተው ትልቅን ህልም ሰንቀው ትምህራተቸውን ገና ከእውቀቱ መቋደስ እንደ ጀመሩ በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ትምህታቸውን ሲያጡ ወላጅ አልባ ሆነው አቀፊያቸውን ቢያጡ መልካምነትነት ትልቅነት መባረክ መስጠት መታደል ነውና አንዱ ሲቸገር ሌላኛው ለእርሱ መድረሱ በሰብዓዊነት አንድ የሚያረገን ስለሆነ ለዚህ ችግር መፍትሄን መስጠት አለብን "50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለ50 ሰው ጌጥ ነው" ብለው በማሰብ ገና በታዳጊ እድሚያቸው ይህንን ችግር በከፊልም ቢሆን ለመቅረፍ ለወገን ዘብ ሊሆኑ እኛ እያለን አንድም ወላጅ አልባ ህፃናት ሊያለቁሱ አይገባም " እኛ እያለን አንድም ወገናችን በችግር ምክንያት ከትምህርቱ ሊስተጓጎል አይገባም" "እኛ እያለን ወገኔ አይታረዝም " በማለት መሰለ መሪቃሉችን በማያያዝ አራሂሙን የልማትና መረዳጃ ማህበር በአዳማ ከተማ ቢሮውን በሬቻ 11 ቀበሌ ጀጁህንፃ ቢሮቁጥር 34 ላይ ግንቦት 8/2011ዓ.ል በውስን ወጣቶች አማካኝነት ህጋዊሰውነት በማግኘት ተመሰረተ::
እኚ ወጣቶች ህጋዊ ሰውነት ሳያገኙ በፊትም ከትምህትር ላይ ከሚተርፋቸው ሳንቲም በመነሳት የተላያዩ ችግርተኞችን ይረዳሉ:: ይህንን የበጎነት ስራ አስፍተው እንደሀገር ለመስራት ከኢ.ፌ.ድ.ሪ የሲቪል ማህበራቶች ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት ሐምሌ 17/2012 በመዝገብ ቁጥር 4894 ተመዝግቦ አራሂሙን በጎ አድራጎት ድርጅት ህጋዊ ሰውነት በማግኘት እንደሀገር ተመሰረተ:: በምስረታ እንቅስቃሴ ሂደትም በርካታ እንቅፋቶችን እና ተግዳሮቶችን ለማሳለፍ ተችሏል::
በነዚህ ሁሉ ውጣ ውረዶች ውስጥ በማለፍ በችግር ውስጥ ያለን ሰው እንደ መርዳት የሚያስደስት ነገር የለምና ያለምንም ቋሚ ፋይናንስ ለተቸገሩ ሰዎች በህይወታቸው ለሚያጋጥሟቸው ችግሮች በሙሉ ከተለያዩ ማህበረሰብ የድጋፍ ማሰባሰቢያ በማድረግ ህይወታቸውን ለማሳመር ጥረት አድርገዋል:: አራሂሙን በጎ አድራጎት ድርጅት ከተመሰረተም በኃላ እንደሀገር እንቅስቃሴ ለማድረግ የተለያዩ መንገዶችን በመንደፍ ለሰውች ቀላል በሆነ መንገድ ትንሽ ትልቅ ወንድ ሴት አዛውንት ሳይል ሁሉም የሚሳተፍበት በስሩ አባላቶችን ሰብስቦ የበጎነት ስራውን ማስፋፋት ተችሏል::
በዚህ በተሳካ መንገድ ሰዎችን አባል በማረግ ከአባላቶች በሚያገኘው ቋሚ ወርሃዊ መዋጮ መሰረት በችግር ላይ የሚገኙ ሰዎችን በተለያዩ መንገድ የመርዳት እንቅስቃሴውን ያደርጋል:: በአራሂሙን በጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ የበጎነት ስራዎች በሚሰሩበት ሂደት ላይ በርካታ ጠንካራ ጎኖችንም በማስተናገድ ላይ ቆይቷል::
ከአንድ ቤተሰብ በፈነጠቀ የበጎነት ብርሃን ለሀገር እንቅስቃሴዎች ለመትረፍ እንዲሁም ለአራሂሙን በጎ አድራጎት ድርጅት ጠንካራም በመሆን ቆይቷል:: በዚህ ጥንካሬ መሰረት ለወገን ደራሽ የመሆን ስራውንም ከአዳማ በማሳደግ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴውንም ወደ አዲስ አበባ እና ወደ ጅማ በማድረስ ላይ ይገኛል::
ከዚህም በኃላ አራሂሙን በጎ አድራጎት ድርጅት ስራውን አስፎቶ እየሰራ ይገኛል በአዲስ አበባ ጀሞ ሁለት ወሊፈን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 111 እንዲሁም አስከትሎ በጅማ ሀጂ ከማል ህንፃ 5ተኛ ፎቅ 105 ቅርንጫፉን በመክፈት በቅርንጫፎቹም አማካኝነት በጥቂቱ ሀገርን ማልማት ላይ የተለያዩ ሚናዎችን እየተወጣ ይገኛል:: ከችግኝ ተከላ እንስቶ አታክልት መንከባከብ ወገኑ በደም ዕጥረት ምክንያት እንዳያልፍ ለመታደግ የደም ልገሳዎችን በማረግ ሚናውን ተወቶዋል:: በትምህርት ዲፓርትመንትም አንድም ልጅ ከትምህርቱ ሊሰተጏጎል አይገባም በማለት የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አዳርጓል:: በተጨማሪም የትምህርት ክፍያቸውን እየሸፈነም በማስተማር ላይ ይገኛል:: በሌላኛው በኩል ደግሞ የተለያዩ ፕሮጀግቶችን በመቅረፅ በእርዳታና ልማት ዲፓርትመንት ስር የተለያዩ ወላጅ አልባ ልጆችን፣ ችግርተኞችን፣ አዛውንቶችን፣ ተፈናቃዮችን እና ህሙማንን በተለያዩ ግዜያት በመርዳት ላይም የበጎነት አሻራውን እያስቀመጠ ይገኛል:: አንድም ወገናችን እኛ እያለን በራህብ ምክንያት አይሞትም በማለት እንዲሁም በየወሩ አዛዎንቶችን በመጎብኘት አብሯቸው ደስታን እሚሞሉ ቆይታን በመስጠት የቤት እድሳትንም እያደረገ በ2012 እና በ2013 ብቻ ከ1031 ቤተሰቦች በላይ ረድቷል:: እንዲሁም እንደሀገር በነበረው በነፍስ አድን ጥሪውም ላይ ለእህታችን ሀያት ኢብራሂም ከ2 ሚልዮን ብር በላይ የገቢ ማሰባሰብያ ፕሮግራሙን እጅግ በተሳካ ሁኔታ መፈፀምም ተችሏል::
ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው በሚለው መርህ በመመራት ለእህታችን ሀያት ኢብራሂም ለህክምናም ከ2 ሚልየን ብር በላይ ለተጠየቅችው በስድስት ቀን በተደረገው የገቢ ማሰባሰብያ ፕሮግራም በየአስፓልቱ በየከተማው በየሱቁ በየ አደባባዩ ደከመን ሰለቸን ውሃጠማን ሳይሉ ጠዋት ወተው ማታ እየገቡ አንድ ሆነው ሀይማኖት ፆታ ሳይለያቸው በጣም ግሩምና አስደሳች በሆነ መልኩ የሀያትን መዳን ጓግተው ተስፋ ሰንቀው በመለመን 1 ብር ለሀያት እያሉ ከ550 ሺህ ብር በላይ በማሰባሰብ ድጋፍ አርገዋል:: በተመሳሳይ መልኩም ጁማ ቅርንጫፍ ላይ አስተዋፆውን በማድረግ ለዚያም ከጅማ university የምስክር ወረቀትን ማግኘት ተችሏል:: ህልማቸውና ግባቻው ወገናቸውን ከችግር ማላቀቅ ደስተኛ ህይወትን እንዲኖራቸው ማረግ ነው። የጎዳና ተዳዳሪዎችን መታደግ በተቻለው አቅም መታደግ የነገን ትውልድ ማፍራት ነው:: እነዚህንና መሰል የበጎ ስራዎችን አስፍቶ ለመስራት በ2013 ትልቅን ፕሮጀክት በመንደፍ ሁሉንም አቀፍ መጠለያን የያዘን መአከል ለመግንባት ለህሙማን፣ ለወላጅ አልባ ህፃናቶች፣ ለተፈናቃዮች፣ ለአዛውንቶች ተግቶ እየሰራ ይገኛል:: በ2013 ኣመት መጫረሻ ላይም የብዙ ግዜ እቅዱና ህልሙ የነበረውን ሁለ ገብ ማዕከል ባሉት ቆራጥ ልጆቹና ቆራጥ አባሉቹ ትልቅ መሰዋትነትን በመክፈል ሁሉም የቻሉትን ርብርብ በማረግ እንደ አዳማ የመጀርያቸውን ማአከል መክፈት ተችለዋል::
በዚህ ማአከል ውስጥም የላይብረሪ አገልግሎት፣ የኮንፒውተር ስልጠና፣ የተለያዩ የዲን እና የአካዳሚ ኮርሶችን እንዲሁም የልጆች ቂርአትና ተርቢያን ጨምሮ የመሰሉ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል። በ2014 እና 2015 በሶስቱም ቅርንጫፉ ከ6000 በላይ ለሚሆኑ ሰውች የተለያየ ድጋፍን ማድረግ የቻለ ሲሆን ። በቴክኖሎጂው ዘርፍ ደሞ መስረታዊ የኮምፒተር በ5ዙር 300 ተማሪዎች በላይ አስተምሮ በማስመረቅ ከቴክኖሎጂ ጋር ማስተዋወቅ ችሏል ። ለዚህ ማአከል የኪራይ ክፍያ ይውል ዘንድ የተለያዩ የቢዝነስ አይዲያዎችን በመፍጠር ዛሬ ላይ የቺፕስ ስራ በስፋት እየሰራ ይገኛል:: ይህም ስራ በጣም ትልቅ አሻራን በመጣል ዛሬ ድረሰም ማዕከሉ ፀንቶ እንዲቀጥል በታሪክ ትልቅን አሻራን ማስቀመጥ ተችለዋል:: በነዚህ ሁሉ የስራ ሂደትም ውስጥ የሚኖሩ ክፍተቶችም አሉ::
እነዚህን ሁሉ ክፍተቶችን ለመድፈን እኛም ተነስተን ከአራሂሙን በጎ አድራጎት ድርጅት ጎን በመቆም በቻልነን አቅም በገንዘብ : በእውቀት እንዲሁም በሞያ አገልግሎት በመስጠት የጀርባ አጥንታቸው ልንሆን ይገባል። እኚህ ወጣቶች አንድ ሆነው ገና በተማሪ አቅማቸው እንዲህ ከሰሩ ባለ ሀብቶች አቅሙ ያላችሁ እናትና አባቶች ከዚህ በላይ እንዲሰሩ እጅና ጏንት ሆነን ልናግዛቸው ይገባል:: እኔ፣ አንተ፣ አቺ፣ እናንተ፣ እኛ፣ በአንድ ላይ በጋራ በመሆንም የአራሂሙን በጎ አድራጎት ድርጅትን ኣላማ ከግብ እንዲደር የማድረግ ኃላፊነት አለብን::
የአራሂሙን በጎ አድራጎት ድርጅት ኣላማ ከግብ እንዲደርስ ቀላል በሆነ መንገድ ትንሽ ትልቅ ወንድ ሴት አዛውንት ሳይል ሁሉም አባል 1ኛ 1000 ብር 2ኛ 500 3ኛ 200 4ኛ100 5ኛ 50 6ኛ 20 እንዲሁም -በሞያ እውቀት #እኛ እያለን አንድም ወገናችን ፣ አይራብም ፣ አያለቅስም ብለን ከንግግርም አልፈን በተግባር ተሻግረን ከለን ላይ ቀን ሰን አካፍለን በመልካሙም ብችግርም ግዜ እደ ብረት ጠንክረን እርስ በእርስ እየተደጋገፍን ከአዳማ ተስተን አዲስ አበባና ጅማን ይዘን ወገኖቻችንን አስተባብረን ቀጣይ ቅርንጫፎቻችንን አስፍተን ለተቸርሩ ወገኖቻችን ለጭንቃቸውና ለሀዘናቸው ዘብ ፣ ምሶሶ፣ ማሀገር እንሆናለን ። ሀዘናቸው ወደ ደስታ ትካዜያቸውን ወደ ለመለመ ተስፋ እንለወጠዋለው ። አራሂሙን በጎ አድራጎት እንደ እንደ ሀገርና እንደ አለም ከፍ እናረገዋለን ችግርን ድል እንነሳለን ለብዙ ህፃናቶ ስኬትና ትልቅ ደረጃ መድረስ ለህመምተኞና ለአዛውንቶች መድሆን ለመሆን ተግተን ጠንክረን ደከመን ሰለቸን ሳንል እንሰራለን አላህ ላይም ተወክለን ኢስቲኣናውን እንለምናለን ትልቅ እናልማለን የረሱልን ግሩርብትናም በጀነትን እንሻለን ።
© 2023 Arrahimun Charity Organization. All rights reserved.